የእንጀራ አሰራር

ከመጸሃፉ "Taste of Ethiopia"

ከአገር ውጭ እንጀራ ለመጋገር የዳበረ ልምድ የሚደባለቁት ተእህል አይነቶችና መጠኖች፤

- ሁለት ብርጭቆ የጤፍ ዱቄት
- ሁለት ብርጭቆ ነጭ የስንዴ ወይንም የገብስ ዱቄት
- አንድ ተኩል የስኳር ምንኪያ ቤኪይንግ ፓውደር
- አምስት ብርጭቆ ሞቅ ያለ ውሃ

  1. የጤፍ ዱቄቱ በሁለት ተኩል ብርጭቆ ውሃ ተቦክቶ ይቀመጣል።
  2. የስንዴው ወይም የገብሱ ዱቄት ግማሸ የስኳር መንኪያ ቤኪይንግ ፓውደር ይገባበትና በብሌንደር ውስጥ ተዋህዶ በሳህን ውስጥ ይቀመጣል።
  3. ሁለቱ ቡኮዎች ተከድነው ከ2 እስከ 3 ቀን እንዲያቀሩ ይቀመጣሉ።
  4. ቀኑ ከደረስ በኋላ ቀስ ተብሎ የቀረረውን ውሃ ከሁለቱም ሳህኖች ውስጥ ማፍሰስ።
  5. ሁለቱም እህል (ጤፍ እና ስንዴ/ገብስ) አቀላቅሎ መለውስና እህሉ ኩፍ እስኪል ድረስ ለ2 ሰዓት ያህል ማስቀመጥ።
  6. ከዚያ በኋላ 425 ዲግሪስ ፍ በሞቀ መጋገሪያ አየር እንዳይገባ ቶሎ እየከደኑ እንጀራውን መጋገር።